ምዕራፍ 11

1 እኔም፣ ሜዶናዊ ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪው ዓመት እርሱን ለማገዝና ለማበርታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር፡፡ 2 አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ ሦስት ሌሎች ነገስታት በፋርስ ይነሳሉ፤ አልተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፡፡ በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግስት ላይ ያስነሣል፡፡ 3 ከዚያም በታላቅ ኃይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ሃይል ንጉስ ይነሣል፡፡ 4 በኃይሉ እየገነነ ሳለም፣ መንግስቱ ይፈርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፍሳትም ይከፋፈላል፡፡ መንግስቱ ተወስዶ ለሌሎች ስለሚሰጥ ለዘሩ አይተላለፉም፤ ኃይሉም እንደ መጀመሪያው አይሆንም 5 የደቡብ ንጉስ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፣ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል፡፡ 6 ከጥቂት ዓመታት በኋላም አመቺ ጊዜ ሲያገኙ አንድነት ይፈጥራሉ፡፡ የደቡብ ንጉስ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉስ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ኃይሏን ይዞ መቆየት አትችልም፤ በእነዚያ ቀናት እርሷ ከቤተ መንግስት አጃቢቿ፣ ከአባቷና ከደጋፊዎቿ ጋር አልፋ ትሰጣለች፡፡ 7 ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሳል፤ የሰሜኑን ንጉስ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋር ተዋግቶ ድል ያደርጋል፡፡ 8 አማልክታቸውን፤ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከክብርና ከወርቅ የተሰሩ የክብሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካሉ፤ ወደ ግብፅም ይወስዳል፡፡ ለጥቂት ዓመታም ከሰሜኑ ንጉስ ጋር ከመዋጋት ይቆጠባል፡፡ 9 የሰሜኑም ንጉስ፣ የደቡቡን ንጉስ ግዛት ይወራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡ 11 ከዚያም የደቡቡ ንጉስ በቁጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉስ ይወጋል፡፡ የሰሜኑ ንጉስ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ሰራዊቱ ለደቡብ ንጉስ አልፎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 12 ሰራዊቱ በሚማረክበት ጊዜ ልቡ በትዕቢት ይሞላል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ይገድላል፤ ነገር ግን በድል አድራጊነቱ አይጸናም፡፡ 14 በዚያም ዘመን ብዙዎች በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሣሉ፡፡ ራዕዩ ይፈጸም ዘንድ ከህዝብህ መካከል ዐመፀኛ የሆኑ ሰዎች ይከሣሉ፤ ነገር ግን ተሰነካክለው ይወድቃሉ፡፡ 15 የሰሜኑም ንጉስ መጥቶ የዐፈር ድልድል ይክባል፤ የተመሸገእውንም ከተማ ይይዛል፡፡ የደቡቡ ሰራዊትም ለመቋቋም ኋይል ያጣል፤ የተመረጡት ተዋጊዎቻቸው እንኳ ፀንተው መዋጋት አይችሉም፡፡ 16 ነገር ግን የሰሜኑ ንጉስ በደቡቡ ንጉስ ላይ ደስ ያሰኘውን ያደርጋል፤ ማንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡ በመልካሚቱ ምድር ላይ ይገዛል እርሷን ለማይፋትም ኋይል ይኖረዋል፡፡ 17 የሰሜኑ መንግስት ያለውን ሠራዊት ሁሉ ይዞ ለመምጣት ይወስናል፤ ከደቡቡም ንጉስ ጋር ይስማል፣ የደቡቡንም መንግስት ለመጣል ሴት ልጁን ይድርለታል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም፤ ያሰበውም ነገር አይጠቅመውም፡፡ 18 ከዚህም በኋላ በባሕር ጠረፍ ወዳሉት አገሮች ፊቱን በመመለስ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ አዛዥ ትዕቢቱን ያከሸፍበታል፤ በራሱም ላይ ይመልስበታል፡፡ 19 በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ደግሞም አይታይም፡፡ 20 በእርሱ ቦታ የሚተካውም የመንግስቱን ክብር ለማስጠበቅ የሚውል ግብር እንዲከፍል የሚያስገድድ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በቁጣ ወይም በጦርነት ሳይሆን በጥቂት ዓመታ ውስጥ ይደመሰሳል፡፡ 21 በእርሱም ፋንታ የተናቀ ሰው የነግሣል፤ ለእርሱም ሕዝቡ ንጉሳዊ ክር አይሰጡትም፣ በቀስታ ይገባና በተንኮል መንግስቱን ይዛል፡፡ 22 ከፊቱ የሚቆመው ሰራዊት እንደ ጎርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡ ሰራዊቱና የቃል ኪዳኑም አለቃ ሳይቀር ይደመሰሳሉ፡፡ 23 ከእርሱ ጋር ስምምነት ከተደረገ በኋላ የማታለል ስራውን ይሰራል፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር በብርታት እየጨመረ ይሄዳል 24 የበለጸጉትን ክፍለ አገሮች በሰላ ሳሉ በድንገት ይወሯቸዋል፤ አባቶቹም ሆኑ አያቶቹ ያላደረጉትን ነገር ያደርጋሉ፤ ብዝበዛውን ምርኮውንና የተገኘውን ሀብት ሁሉ ለተከታዮቹ ያካሏቸዋል፤ ምሽጎችን ለመጣል ያሤራል፤ ይህን የሚያደርገውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ 25 “ታላቅ ሠራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሳሳል፤ የደቡብ ንጉሱም ብርቱ የሆነ ኃይል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ከር ግን ከተዶለተበት ሴራ የተነሳ መቋቋም አይእል፣፡፡ 26 ከንጉስ ማዕድ አብረውት ሲበሉ የነበሩት፤ ብዙዎቹም በጦርነት ይገደላሉ፡፡ 27 አንዳቸው በሌላኛው ላይ ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለት ነገስታት፣ በአንድ ገበታ አብረው ይቀመጣሌ፤ እርስ በእርሳቸውም በከንቱ ውሸት ይነጋገራሉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜ የሚሆነው በተወሰነው ጊዜ ነው 29 በተወሰነው ጊዜ ይመለስና ደቡቡን እንደ ገና ይወርራል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ውጤቱ ከበፊቱ የተለየ ይሆናል፡፡ 30 የኪቲም መርከቦች ይቃወሙታል፤ ልቡም ይሸበራል፡፡ ወደ ኋላም ይመለሳል፤ ቁጣውን በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይወርዳል፤ ተመልሶም የተቀደሰውን ኪዳ የተዉትን ይንከባከባል፡፡ 31 የጦ ሠራዊቶቹም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘውትሩንም መስዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ፍፁም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ፤ 32 ኪዳኑን የሚተላለፉትን በማታለል ይስታል ይረክስባቸዋልም፤ አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ግን ደንተው ይቃወሙታል፤ ርምጃም ይወስዳሉ፡፡ 33 “ለጊዜው በሰይፍ ቢወድቁም፣ ቢቃጠሉም፣ ቢማረኩና ቢዘረፉም፣ ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብዙዎችን ያስተምራሉ፡፡ 34 በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ ርዳታ ይገኛሉ፤ እውነተኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎችም ይተባበሯቸዋል፡፡ 35 ጥበበኛ ከሆኑ ሰዎች አንዳንዶቹ ይሰናከላሉ፣ ይህም እስከ ፍፃሜ ዘመን ድረስ የጠሩ፣ የነጠሩና እንከን የሌለባቸው ይሆን ዘንድ ነው፤ የተወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰምና፡፡ 36 ንጉሱ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አማላክ ላይ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፤ የቁጣውም ዘመን እስኪፈጸም ይሳካለታል፤ የተወሰነ ነገር ሁሉ መሆን አለበትና። 37 ሴቶች ለሚወዱትም ሆነ ለአባቶቹ አምላክ ትክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል። 38 በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያደብራል፤ አባቶቹ የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል። 39 በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽቶችን ይወጋል፤ ለእርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከበራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ልያ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል። 40 “በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥም ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሰርጎች በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወራል፤ እንደ ጎርም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል። 41 የከበረችውንም ምድር ይወራል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩእስራኤላውያንም ተሰነካክለው ይወድቃሉ፣ ነገር ግን ከኤዶም፣ ከሞዓብ ብዙ ሰዎች እንዲሁም ከአሞን የቀሩት ሕዝብ ከእጁ ያመልጣሉ። 42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል ግብፅም አታመልጥ። 43 የወርቅና የብር ክምችትን፣ እንዲሁም የግብፅን ሀብት ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል፤ የሊቢያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይገዙታል። 44 ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል። 45 ንጉሣው ድንኳኖቹን በባሕሮች መካከል ውብ በሆነው ቅዱስ ተራራ ላይ ይተክላል፤ ይሁን እንጂ ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ ማንም አይረዳውም።