1 በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጾጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ። 2 በምድር አፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጉስቁልና ይነሣሉ። 3 ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። 4 ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ዕውቀትም ይበዛል። 5 እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር። 6 ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጽሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው። 8 እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ ጌታዬ፣ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። 9 9 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለሆነ ሂድ፤ 10 ብዙዎቹ ይነጻሉ፤ ይጠራሉ እንከን አልባምይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይድናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፣ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ። 11 “የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ፍጹም ጥፋት የሚያመጣው አስጸያፊ ርኵሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል። 12 የሚታገሥና እስከ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሰለሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው። 13 “አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ድረስ ሂድ፣ ታርፋለህ፤ በቀኖች መጨረሻም ተንሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”