1 እኔ፣ ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ ጽፌያለሁ፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆንኩ እኔ ጳውሎስ ነኝ፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች በእርሱ ይበልጥ እንዲታመኑ ለመርዳት ሰራሁ፡፡ እግዚአብሔር እኛ ሁላችንንም የእርሱ እንድንሆን መረጠን፤ እኔ ደግሞ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዲኖሩ ልረዳቸው ሰራሁ፡፡ 2 የእርሱ ህዝቦች እንዴት እንደዚህ እንደሚኖር መማር ይችላሉ፣ ምክንያቱም እነርሱ እግዚአብሔር ለዘላለም እንዲኖሩ እንደሚያደርጋቸው እርግጠኞች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሀሰት አይናገርም ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ እንኳን፣ ለዘለዓለም ሊያኖረን ቃል ገብቷል፡፡ 3 ከዚያም፣ በትክክለኛው ጊዜ ሁሉም እንዲረዳው ቃሉን ግልጽ አደረገ፡፡ ምክንያቱም እርሱ ይህን መልዕክት እንድሰብክ እኔን አምኖኛል፡፡ እኔ ይህን የማደርገው ያዳነንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመታዘዝ ነው፡፡ 4 ቲቶ አንተ ለእኔ እንደ ልጄ ስለሆንክና ሁለታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ስለምናምን እኔ እጽፍልሃለሁ፡፡ ከአባታችን እግዚአብሔር እና ከአዳኛችን ክርስቶስ ኢየሱስ ለአንተ መልካምነትንና ሰላም ይሁን፡፡ 5 በዚህ ምክንያት በቀርጤስ ደሴት ተውሁህ፤ ይኸውም ያልተጠናቀቀውን ስራ እንድትሰራ በእያንዳንዱ ከተማ ለሚገኙ አማኞች ሽማግሌዎችን ልክ እኔ እንድታደርገው በነገርኩህ መሰረት እንድትሾም ነው፡፡ 6 የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ነቀፋ የሌለበት መሆን ይገባዋል፡፡ አንዲት ሚስት ብቻ ልትኖረው፣ ልጆቹ በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ እና ሰዎች የእርሱን ልጆች ባለጌ ወይም የማይታዘዙ አድርገው የማይቀጥሯቸው ሊሆን ይገባዋል 7 የእግዚአብሔርን ህዝብ የሚመራ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት እንደሚያስተዳደር ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ጥሩ ምስክርነት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ የሚኮራ መሆን የለበትም፣ በቶሎ የሚቆጣ እና በምንም አይነት ምክንያት ተቆጥቶ የሚቆይ መሆን ያለበትም፡፡ ሰካራም መሆን የለበትም፤ ጠብና ክርክርን ሚወድ እንዲሁም ስግብግብ ሰው መሆን የለበትም፡፡ 8 ከዚህ ይልቅ፣ እንግዶችን፣ በመልካም የሚቀበል እንዲሁም መልካም ነገሮችን የሚወድ መሆን አለበት፡፡ ሁልጊዜም ራሱን የሚገዛና ታማኝ፤ ሁልጊዜም እውነትን የሚናገር፣ እና ሌሎች ሰዎችን በስርዓት የሚያስተናግድ መሆን አለበት፡፡ ነገሮችን ሲያደርግ ሁልጊዜም ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ማሰብ አለበት፣ ደግም ከኋጢአት መራቅ አለበት፡፡ 9 ሁልጊዜም ከእኛ የተማራቸውን እውነተኛ ነገሮች ማመን አለበት፣ ደግሞም በተማረው መሰረት መኖር አለበት፡፡ ሰዎች በትምህርቱ መሰረት እንዲሆኑ ለማድረግና በተማሩት መሰረት ለመኖር የማይፈልጉ ሲሆኑ እነርሱን ለማስተካከል ትምህርቱን በኑሮው ማሳየት መቻል አለበት፡፡ 10 እነዚህን ነገሮች እነግራችኋለሁ፣ ምክንያቱም ማንም ሰው ተው እንዲላቸው የማይፈልጉ፣ በተለይ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ እንዲገረዙ የሚናገሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የሚናገሩት ምንም እርባና የለውም ሰዎች እየታለሉ የተሳሳቱ ነገሮችን እንዲያምኑ ያግባባሉ፡፡ 11 እናንተና የሾማችኋቸው መሪዎች፣ እማኞችን እንዳያስተምሩ መከልከል አለባችሁ፡፡ የሚያደርጉትን ለማስተማር ምንም መብት የላቸውም፡፡ እነዚህን ነገሮች የሚያስተምሩት ሰዎች ገንዘብ እንዲሰጧቸው ነው፡፡ ይህ በጣም አሳፋሪ ነው! መላው ቤተሰቦች የተሳሳቱ ነገሮችን እንዲያምኑም ምክንያት ይሆናሉ፡፡ 12 የገዛ ሰዎቹ ነብይ ነው የሚሉት አንድ የቀርጤስ ሰው፣ “የቀርጤስ ሰዎች ሁልጊዜም እርስ በእርሳቸው ይወሻሻሉ! እነርሱ እንደ አደገኛ የዱር እንስሳ ናቸው! ሰነፎችና ሁልጊዜም ብዙ ምግብ የሚመገቡ ናቸው” ብሏል፡፡ 13 ይህ ሰው የተናገረው ዕውነት ነው፣ ስለዚህ በግድ አስተካክሏቸው፡፡ ይህ ሲሆን ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ ነገሮችን ልታስተምሯቸውና ሊያምኑ ይችላሉ፡፡ 14 እነዚህ ሰዎች ትርጉም የለሽ በሆኑ የአይሁድ ተረቶችና ከእግዜሔብርን ሳይሆን ከሰዎች በሚመጡ ትዕዛዞች ጊዜ ሊያጠፉ አይገባም፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእውነቱ ፊታቸውን የመለሱ ናቸው፡፡ 15 አንድ ሰው ኃጢአተኛ አስተሳሰብ ወይም ፍላጎት ከሌለው፣ ሁሉንም ነገሮች በበጎ ይመለከታል ነገር ግን ማንም ሰው ክፉና በክርስቶስ ኢየሱስ የማያምን ከሆነ፣ ሁሉም ነገር ያረክሰዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በቆሻሻ መንገድ ያስባሉ፣ እናም በክፉ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ይወሰናሉ፡፡ 16 እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ ቢናገሩም እንኳን፣ ስራቸው ግን እርሱን እንደማያውቁ ያሳያል፡፡ ሌሎች ሰዎች አስጸያፊ ሆነው ያገኟቸዋል እግዚአብሔርን አይታዘዙም ለእርሱ ምንም መልካም ነገር ማድረግ አይችሉም፡፡