ምዕራፍ 1

1 እኔ፣ ጳውሎስ በፊልጵስዮስ ለምትኖሩ የተወደዳችሁ አማኞች ይህን ደብዳቤ እጽፍቿለሁ፡፤ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች የሆንን እኔ ጳውሎስ እና ጢሞቴዎስ ይህን ደብዳቤ ልከንላችኋል፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁና እግዚአብሔር ለራሱ ለለያችሁ፣ ለእናንተ በፊልጵስዮስ ላላችሁ ሁሉ ይህን ጽፈን ልከንላችኋል፡፡ በዚያ ለምታገለግሉ ዋጋ አገልጋዮችና ዲያቆናት ይህን ደብዳቤ ልከናል፡፡ 2 ከእግዚአብሔር አባታችን እና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ጸጋ እንዲበዛላችሁና ሰላም እንዲሆንላችሁ እንጸልያለን፡፡ 3 ስለ እናንተ ባሰብኩ ቁጥር እግዚአብሔር አምላኬን በጸሎቴ አመሰግናለሁ፡፡ 4 ለእናንተ ሁልጊዜም በደስታ እጸልለሁ 5 ደግም ካመናችሁበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ከጢሞቴዎስ፣ ከእኔና ከሌሎች ጋር የምስራአቹን በመስበክ አብራችሁን እየሰራችሁ ስላላችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ 6 እግዚአብሔር በመካከላችን በጣም መልካም ነገሮችን እያደረገ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስበት ጊዜ ድረስ እነዚህን የጀመራቸውን ነገሮች እንደሚጨርስ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ 7 ስለእናንተ እንደዚህ ማሰቤ ትክክል ነው ምክንያቱም ከልቤ እወዳችኋለሁ፡፤ እግዚአብሔር በበጎነቱ እንዳከናውነው የሰተኝን ሥራ አሁን እዘህ በእስር ላይ ሆኜም ሆነ ወይም በአደባባይ የምስራቹን ስናገርና ለሰዎች ወንጌል እውነት መሆኑን ስገልጽ ከጎኔ ነበራችሁ፡፡ 8 ሁላችሁም ከልቤ እንደምወዳችሁና፣ ክርስቶስ ኢየሱስ በርህራሄ ሁላችንም እንደሚወደን እንደዚሁ ምን ያህል ከልቤ ከእናንተ ጋር መሆን እንደምፈልግ እግዚአብሔር ይመለከታል፡፡ 9 እርስ በእርሳችሁ ከፊት ይልቅ ይበልጥ እንድትዋደዱና፣ እግዚአብሔር ለምን ይህን እንድታደርጉ እንደሚፈልግ እንድታውቁ እንድትረዱ ለእናንተ እጸልያለሁ፡፡ 10 ምን ማመን እንዳለባችሁ እንድታውቁ እግዚአብሔር እንዲረዳችሁና ማድረግ የሚገባችሁን እጅግ በተሸለ መንገድ ማድረግ እንድትችሉ እጸልያለሁ፡፡ ክርስቶስ ሲመለስ ቅኖችና ያለነቀፋ መሆን እንድትችሉ ይህን እጸልያለሁ፡፡ 11 በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት እግዚአብሔር በፊቱ ተቀብላችኋልና ሁልጊዜም ማድረግ የምትችሉትን እንድታደርጉ እጸልያለሁ፡፡ ይህ ሲሆን ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔርን እንዴት እንደምታከብሩ ማየት ይችላሉ፡፡ 12 አማኝ ወገኖቼ፣ ማናቸውም መከራ ወንጌልን ለሰዎች ከመስበክ እንዳልከለከለን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፤ ይልቁንም፣ መከራዎቼ ብዙ ሰዎች ስለ ክርስቶስ የምስራቹን እንዲሰሙ አስችለዋል፡፡ 13 በተለይም እዚህ ሮም ውስጥ ያሉ ጠባቂ ወታደሮች እና በከተማዋ ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች ስለ ክርስቶስ የምስራቹን በመስበኩ ምክንያት እስረና እንደሆን አውቀዋል፡፡ 14 እንደዚሁም፣ በዚህ የሚገኙ ብዙዎቹ አማኞች ከፊት ይልቅ በድፍረትና ያለፍርሃት የምስራቹን ይሰብካሉ ምክንያቱም ጌታን ይበልጥ በጥንካሬ አምነዋል፡፡ ስለ ኢየሱስ በልበ ሙሉነት ይናገራሉ ምክንያቱም የምስራቹን በእስር ቤት ውስጥ እንድናገር ጌታ ሲረዳኝ አይተዋል፡፤ 15 አንዳንድ ሰዎች ቅናተኞች ስለሆኑና ከእኔ ይልቅ እነርሱን እንዲያከብሯቸው ስሚፈልጉ የምስራቹን ይሰብካሉ፡፤ ሌሎ ግን ክርስቶስን ስለሚወዱና ወንጌልን ያልሰሙ ወንጌልን እንዲሰሙ ብለው ይሰብካሉ፡፡ 16 ክርስቶስን ስለሚወዱ ወንጌልን የሚሰብኩና እግዚአብሔር ወንጌልን እንድሰብክ እንደሾመኝ ያውቃሉ እነዚህ ወንጌል እውነት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ 17 በራስ ወዳድነት ምክንያት ወንጌልን የሚሰብኩ ግን ይህን ለማድረግ መልካም ምክንያት የላቸውም እዚህ እስር ቤት ውስጥ ሆኜ ይበልጥ መከራ የሚጨመርብኝ መስሏቸው ይሰብካሉ፡፡ 18 ነገር ግን ይህ ምንም ማለት አይደለም1 በመልካም ምክንያቱም ይሁነ በመጥፎ ሰዎች ወንጌልን እየሰበኩ ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምስራቹን እያስፋፉ ስለሆነ እጅግ ደስ ብሎኛል! በዚህም ደስታዬ ይጨምራል! 19 እግዚአብሔር ከእስር ነጻ እንደሚያወጣኝ ስለማውቅ ደስ ይለኛል፡፡ እናንተ እየጸለያችሁ ስሆነና የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ እየረዳኝ ስለሆነ እርሱ ይህን ያደርጋል፡፡ 20 በማናቸውም አይነት መንገድ ማሰራትያለብኝ ሳልሰራ እንደማልቀር በጉጉትና በልበ ሙሉነት እጠባበቃለሁ፡፡ ይልቁንም፣ ቀድሞ እንደነበረኝ አሁንምብርታቱ አለኝ፡፡ በህይወት ብኖር ወይንም ብሞት ክርስቶስን በስጋዬ አከብረዋለሁ፡፡ 21 እኔ የምኖረው ክርስቶስን ለማክበር ነው፡፡ ነገር ግን ብሞትም እንኳንና ይህ ይበልት ይሻለኛል፡፡ 22 በሌላ በኩል፣ በዚህ አለም በአካሌ ውስጥ መኖሬን ብቀጥል፣ በዚህ ሰዎች ክርስቶስን ማገልገሌን መቀተል እችላለሁ፡፡ ስለዚህ ከመኖር ወይም ከመሞትን የትኛውን እንደምንመርጥ አላውቅም፡፡ 23 የትኛው እንደሚሻለን መምረጥ አልችልም፣ መኖር ወይም መሞት ሞቼ ይህን ዓለም ትቼ ከክርስቶስ ጋር ለመሆን መሄድን እመኛለሁ፣ ምክንያቱም ለማንም ቢሆን ከክርስቶስ ጋር መሆን እጅግ የተሸለ ነው፡፡ 24 ነገር ግን እዚህ በምድር ላይ መኖሬ ደግሞ ይበልጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁንም እንድረዳችሁ ትፈልጉኛላችሁ፡፤ 25 በዚህ ነገር እርግጠኛ ስለሆንኩ፣ ደስ ለመሰኘት እንድረዳችሁና ክርስቶስን ይበልጥ እንድታምኑት ከእናንተ ጋር በህይወት መኖሬ እንደሚቀትል አውቃለሁ፡፡ 26 ስለዚህ ከክርስቶስ ኢየሱስ የተነሳ ዳግም ከእናንተ ጋር ስሆን ስ እኔ ደስተኛ ልትሆኑ ይገባል፡፡ 27 ከሁም በላይ ደግሞ፣ በዙሪያችሁ በመኖሩ ሰዎች መሀል ስ ክርስቶስ የምስራቹን በሚያከብር መንገድ ኑሩ፡፡ መጥቼ ባያችሁም ባላያችሁም ይህንን አድርጉ፣ አኗኗራችሁ እኔን ደስ ያሰኘኛል፡፡ ሁላችሁም የምስራቹ ወንጌል እንደሚያስተምረን እንደምታምኑና እንደምትኖሩ የተቻላችሁን እንደምታደርጉ ሌሎች ስለ እናተ ሲናገሩ መስማት እፈልጋሁ፡፡ 28 ተቃዋሚዎቻቸችሁ አያስፈሯችሁ! ብርቱዎች ስትሆኑና ስትቋቋሟቸው ይህ እግዚአብሔር እነርሱን እንደሚያጠፋና እናንተን እንደሚያድን ያሳያቸዋል፡፡ 29 እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም ነው ለክርስቶስ መከራን እንድትቀበሉ እንዲሁም በእርሱ እንድታምኑ ለእናንተ ይፈቅዳል፡፡ 30 እኔ በፊልጵስዮስ እንደዚህ ያሉ ሰዎችን እንደተቋቋምኩ መልካሙን የምስራች የሚቃወሙትን ልትቋቋማቸው ይገባል፣ ልክ እንደሰማችሁት እንደዚህ ያሉ ሰዎችን አሁን እዚህ ልቋቋማቸው ይገባል፡፡