ምዕራፍ 1

1 እኔ በእርስር ላይ ያለሁ ጳውሎስ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን የማገለግል ነኝ፡፡ አማኝ ከሆነው ከወንድማችን ጢሞቲዎስ ጋር በዚህ አለሁ፡፡ ይህን ደብዳቤ ለተወደድከው ወንድማችንና አብረኸን ለምትሰራው ፊልሞና እጽፍልሀለሁ፡፡ 2 ደግሞም ለአማኝ እህታችን አፍብያ፣ እና ከእኛ ጋር ልክ እንደወታደር ሆኖ ለሚያገለግለው ለኦርክጳ ይህን ደብዳቤ እጽፋለሁ፡፡ እንደዚሁም በአንተቤት ለሚሰበሰቡት አማኝ ወገኖች እጽፍላቸዋለሁ፡፡ 3 አባታችን እግዚአብሔር እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችሁም በመልካምነቱ መስራቱን እንዲቀጥል እጸልያለሁ፡፡ ስላሙንም አብዝቶ እንዲሰጣችሁ እፀልያለሁ፡፡ 4 ለአንተ ሰጸልይ ፣ ሁልጊዜም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣ 5 ምክንያቱም በጌታ ኢየሱስ እንዴት እንደምታምን ሁልጊዜም እሰማለሁ፡፡ ደግሞም አማኞችን ሁሉ እንዴት እንደምትወድና እንደምትረዳ እሰማለሁ፡፡ 6 እኛ በክርስቶስ እንደምናምን በተመሳሳይ መልክ ሰለምታምን፣ ስለ ክርስቶስ ለአንተ ልንሰጥህ የምንችለውን ማንኘውንም መልካም ነገር ለማወቅ እንድትችል እጸልያለሁ፡፡ 7 የተወደድከው ወዳጄ፣ አንተ የእግዚአብሔርን ሰዎች ትወድ ስለነበረና ስለረዳሀቸው በአንተ ምክንያት እጅግ ደስ ተሰኝቻለሁ፡፡ ደግሞም መጽናናትን አግኝቻለሁ፡፡ 8 ስለዚህ አንዳንድ ነገሮችን እንድታደርግ ልጠይቅህ እወዳለሁ፡፡ ማድረግ የሚገባህን እንድታደርግ አንተን ለማዘዝ ስልጣን እንዳለኝ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ፡፡ 9 ነገር ግን አንተ የእግዚአብሔርን ህዝብ እንደምትወድ ስለማውቅ፣ ይህን እንድታደርግ ከማዘዝ ይልቅ እጠይቃለሁ፡፡ ይህን የምጠይቅህ ከርስቶስን ስላገለገልኩ አሁን እስረኛ የሆንኩ ሽማግሌው የጳውሎስ ነኝ፡፡ 10 ለአናሲሞስ አንድ ነገር እንድታደርግላት እጠይቅሃለሁ፡፡ አሁን እርሱ ለእኔ እንደ ልጄ ነው ምክንያቱም እዚህ እስር ቤት ውስጥ ስለ ክርስቶስ ሰብኬዋለሁ፡፡ 11 ምንም እንኳን እንደምታውቀው የስሙ ትርጉም “ጠቃሚ” ማለት ቢሆንም ቀድሞ ለአንተ የማይጠቅም ነበር፡፡ አሁን ግል ለእኔም ለአንተም ለሁለታችንም ጠቃሚ ነው፡፡ 12 ምንም እንኳን ለእኔ በጣም የተወደደ ቢሆንም ፣ መልሼ ወደ አንተ ልኬዋለሁ፡፡ 13 በአንተ ስፍራ ሆኖ ያገለግለኝ ዘንድ ከእኔ ጋር መሆኑን እወድ ነበር ፡፡ ስለ ክርስቶስ በመስበኬ እስር ላይ በመሆኔ እርሱ ያስፈልገኛል፡፡ 14 ሆኖም፣ አንተን ስላላስፈቀድኩና እርሱ እዚህ ከእኔ ጋር እንዲሆን ፈቃድህን ስላላገኘሁ፣ እዚህ ከእኔ ጋር እንዳይቆይ ወሰንኩ በእርግጥ ልትረዳኝ ከፈለግህ ብቻ ልትረዳኝ እንደሚገባ ወስኛለሁ፡፡ 15 ምናልባት እግዚአብሔር አናሲሞስ ከአንተ እንዲለይ የፈቀደበት ምክንያት ለሁልጊዜም መልስህ ልትወስደው እንድትችል ይሆናል! 16 ከእንግዲህ እርሱ ለአንተ እንደ ባርያ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ፣ ከባርያ እንደተሸለ አድርገህ ትቀበለዋለህ፡፡ እንደ አማኝ ወንድም ይሆንልሃል፣ እርሱ ለእኔ በጣም የተወደደ ነው፣ ነገር ግን ለአንተ በእርግጥ ይበልጥ የተወደደ ይሆናል፡፡ የዚህም ምክንያቱ አሁን እርሱ የአንተ ባርያ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የጌታም ባሪያ ነው፡፡ 17 ስለዚህ እኔና አንተ የእግዚአብሔርን ስራ አብረን እንደምንሰራ ካመንክ እኔን እንደምትቀበለኝ እርሱንም ተቀበለው፡፡ 18 አንዳች ጉዳት አድርሶብህ ቢሆን፣ ወይም የአንተም ዕዳ ቢኖርበት ለዚያ እኔ ኃላፊነቱን ልወሰድ፡፡ 19 እኔ ፣ ጳውሎስ ፣ በገዛ እጄ ጽፌያለሁ፡፡ ከአንተ የወሰደውን እኔ እከፍልሃለሁ፡፡ ለአንተ እንዲህ ማለት እችላለሁ ፣ አናሲሞስ ከአንተ ከወሰደው ይልቅ አንተ የበለጠ የሚገባህን ከፍለሀል፣ ምክንያቱም እኔ ለአንተ የመሰከርኩልህ የራስህን ህይወት እድኗል፡፡ 20 ወንድሜ ሆይ፣ በእርግጥ፣ በጌታ ደስ እንዲለኝ፣ ምክንያት ሆነኽኛል፡፡ ሁለታችንም በክርስቶስ በመሆናችን ልቤን ደስታ ሞልቶታል፡፡ 21 ይህን ደብዳቤ ለአንተ የጻፍኩት፣ እንድታደርግ የጠየቅሁህን እንደምታደርግ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው፡፡ በእርግጥ፣ እንድታደርግ ከምጠይቅህ በላይ እንደምታደርግ አውቃለሁ፡፡ 22 እንዲሁም ፣ የምቆይበትን የእንግዳ ማረፊያ አዘጋጅልኝ፣ ምክንቱም ለእኔ ከጸለያችሁልኝ ጸሎት የተነሳ፣ ከእስር እንደምፈታና ወደ እናንተ እንደምመጣ እርግጠና ሆኜ እጠባበቃለሁ፡፡ 23 በክርስቶስ እየሱስ በመሆኑ ምክንያት ከእኔ ጋር በእስር ቤት መከራ እየተቀበለ የሚገኘው ኤጴፍራ ሰላምታ ያቀርብልሃል፡፡ 24 አብረውኝ ሰራተኛ የሆኑት ማርቆስ ፣አርስጥሮኮስ፣ ዴማስ፣ እና ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፡፡ 25 የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካምነት ለአንተ እንዳይቆረጥ እፀልያለሁ፡፡