ምዕራፍ 1

1 ሙሴም በቅዱስ ድንኳኑ አጠገብ ቆሞ ሳለ ያህዌ ከድንኳኑ ውስጥ ጠራው 2 ለእስራኤል ልጆችም እንድህ ብሎ እንድናገር አዘዘው፡፡ለያህዌ መስዋዕት ስታመጣ ከበግችህ፤ ከፍየሎችህ ወይም ከላሞችህ ውስጥ ይሁን፡፡ 3 የሚታቀርበው መስዋዕት ሙሉ በሙሉ በመሰዊያ የምቃጠል የወይፈን መስዋዕት ከሆነ፥ ምንም አይነት ነውር የሌለበት ልሆን ይገባል፡፡ በያህዌ ፊት ተቀባይነት እንዲያገኝ ወይፈኑንም በቅዱስ ድንኳን ደጃፍ ፊት ታቀርበዋለህ። 4 እጅህንም በመስዋዕቱ ወይፈን ራስ ላይ ትጭናለህ፡፡ ያን ስታደርግ ያህዌ የወይፈኑን የሞት መስዋዕት በፋንታህ የሞቴ እንደሆኔ አድርጎ ይቀበላል፤ የሰራሄውንም ሀጥአትህን ያስተሰሪይልሃል፡፡ 5 ወይፈኑን በያህዌ ፊት ታርደዋለህ፡፡ ከዛም ካህናት የሆኑ የአሮን ልጆች ከደሙ ይወስዱና በቅዱስ ድንኳኑ ደጃፍ አጠገብ በመሰዊያው ሁሉ ላይ ይረጫሉ፡ 6 የወይፈኑን ቆዳ ትገፋለህ፤ ስጋውንም ትቆራርጣለህ፡፡ ሆድቃውና እግሩን ታጥባለህ 7 የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ እንጨት ያስቀምጣሉ፡ እሳትንም ያቀጣጥላሉ፡፡ 8 የወይፈኑን ብልቶች ቆራርጠው ያዘጋጃሉ፤ ራሱን፤ ስቡን በእሳቱ ላይ ያደርጋሉ፡፡ 9 ከካህናቶቹ አንዱ መስዋዕቱ ሙሉ በሙሉ በመሰዊያው ላይ እንድቃጠል ያደርጋል፡፡ የመስዋዕቱ መልካም መዓዛ ለያህዌ ይቀርባል፡፡ 10 የምታቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች ከሆነ፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ታቀርበዋለህ። 11 እንስሳውንም በመሰዊያው አጠገብ በሰሜን አቅጣጫ በያህዌ ፊት ታርደዋለህ፤ ደሙንም በሳህን ትቀበለዋለህ፡፡ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ላይ ይረጩታል። 12 እንስሳውንም በየብልቱ ትቆራርጠዋለህ፡፡ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውኃ ታጥበዋለህ።ከዛም ካህኑ ሁሉን ብልቶች ይቆራርታል፤ ራሱንም ፤ ስቡንም አቅርቦ በመሠዊያው እንጨት ላይ ያቃጥለዋል፡፡ 13 ከካህናቱም አንዱ በመሠዊያው ላይ ባለው በ እንጨቱ እሳቱ ላይ ይረበርበዋል፡፡ የሚቃጠለው መስዋዕት ለያህዌ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል 14 ለያህዌ የሚታቀርበው መስዋዕት ከወፎች ከሆነ፥ መስዋዕቱን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ታቀርባለህ። 15 ካህኑም ወፉን ወደ መሰዊያው ያቀርበዋል፥ ራሱንም ይቈለምመዋል፥ በመሰዊያውም ላይ ራሱን ያቃጥለዋል። ደሙንም በመሰዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፡፡ 16 ከዛም የሆድ ዕቃውንም ከላባዎች ጋር ለይቶ ያስወግደዋል፡፡ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል በአመዱ በምደፋበት ስፍራ ይጥለዋል፡፡ 17 ክንፎቹን ይዞ ወፉን በግማሽ ይቀድደዋል፥ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይከፍለውም። ካህኑም በመሰዊያው እሳት በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ የመስዋዕቱ መልካም መዓዛ በያህዌ ይደርሳል፡፡