የሕልቅያ ልጅ የሆነው ኤርሚያስ የጻፈው መልዕክት ይህ ነው፡፡ እርሱ የብንያም ነገር በሚኖሩበት ዐናቶት ተብሎ በሚጠራ ምድር ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ ካህናት አንዱ ነው፡፡ 2. የዐሞን ልጅ ኢየስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ያሕዌ እነዚህን መልክዕቶች ይሰጠው ጀመር፡፡ 3. የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቁም በነገሠበትም ዘመን ያሕዌ መልዕክቶች ለእርሱ መስጠቱን ቀጥሎ ነበር፤ ሴዴቅያስ ለዐሥራ አንድ ዓመታት በይሁዳ ላይ ንጉሥ ሆኖ እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር መልዕክትን ለእርሱ መስጠትን ቀጥሎ ነበር፡፡ የኢየሩሌም ሕዝብ ወደ ተማርከው ወደ ባቢሎን የተወሰዱት በዚሁ ዓመት በአምስተኛው ወር ነበር፡፡