ምዕራፍ 1

1 ንጉሥ አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞአብ በእሥራኤል ላይ አመጸ፡፡ 2 አንድ ቀን አካዝያ አዲሱ የእሥራኤል ንጉሥ ከላይኛው የቤቱ ሰገነት ወድቆ ቆሰለ፡፡ ስለዚህ መልዕክተኞቹን ጠራና እንዲህ አላቸው የኤክሮን አምላክ ወደሆነው ብዔልዜቡል ሂዱና ከደረሰብኝ የመቁሰል ጉዳት እድን ወይም አልድን እንደሆን ጠይቁ፡፡ 3 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኒቢዩ ኤልያስን እንዲህ አለው ነቢዩ ቲሸቤ ከተማ ውስጥ ነበር የሰማሪያ ንጉሥ መልእክተኞቹን ወደኤክሮን በመላክ ላይ ነው ሂድና እንዲህ በላቸው በእሥራኤል አምላክ ስለሌለ ነው መዳን የምትችል ወይም የማትችል መሆንህን እንዲንግርህ ብዔልዘቡልን የምትጠይቀው 4 እግዚአብሔር ለንጉሥ አካዝያ ከቁሰሉ እንደማይድን በእርግጥ እንደሚሞት ንገረው ይልሀል 5 ስለዚህ ኤልያስ ወደ ምልእክተኞቹ ሄዶ ይህን ስለነገራቸው ወደኤክሮን ከመሄዱ ፋንታ ወደንጉሡ ተመለሱ ንጉሡም እንዲህ በማለት ጠየቋቸው ለምንድነው ፈጥናችሁ የመጣችሁት 6 እንዲህ ብለው መለሱለት አንድ ሰውየ መጥቶ እንዲህ አለን ወደላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ ሂዱና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ንገሩት በእሥራኤል ስለሌለ ነው የምትድን ወይም የማትድን መሆንህ እንዲነግርህ ብዔልዜቡልን የምትጠይቀው ሂዱና ከቁሰሉ የማይድን እንደውም በእርግጥ ይሞታል 7 ንጉሡም እንዲህ አላቸው ወደ እናንተ የመጣውና የሰማችሁትን የነገራችሁ ሰው ምን ይመስላል 8 ከግመል ፀጉር የተሠራ ልብስ ለብሶ በወገቡ ዙሪያ የቆዳ ቀበቶ ታጥቋል አሉና መለሱ፡፡ እርሱ ኤልያስ መሆን አለበት አለ ንጉሡ በመደነቅ 9 ከዚያም ንጉሡ ኤልያስን እንዲይዙት አንድ አዛዥ እና አምሳ ወታደሮችን ላከ ኤልያስን አንድ ኮረታ ጫፍ ላይ ተቀምጦ አገኙት፡፡ አዛዡ ድምፁን ከፍ አደረገና ከኮረብታው ላይ ወደዚህ እንድትወርድ ንጉሡ አዟል አሉ፡፡ 10 ኤልያስ ግን እንዲህ በማለት ለአዛዡ መለሰለት እኔ ነቢይነኝ ስለዚህ እሣት ከሰማይ ወርዶ አንተንና አምሳዎቹን ሰዎችህ እንዲያቃጥል አዝዛለሁ ወዲያው እሣት ከሰማይ ወረደና አዛዡን እንዲሁም አምባዎቹን ወደሮች አቃጠላቸው፡፡ 11 ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ አንድ አዛዥ እና አምሳ ተጨማሪ ወታደሮችን ላከ ኤልያስ ወደነበረበት ሄዱ አዛዡም ነቢዩ በአስቸኳይ ካለህበት እንድትወርድ ንጉሡ ያዝሀል አለ፡፡ 12 ኤልያስ ግን እንዲህ በማለት መለሰ እኔ ነቢይነኝ ስለዚህ እሣት ከሰማይ ወርዶ አንተን እና ወታደሮችህን እንዲበላችሁ አዝዣለሁ ወዲያው ከእግዚአብሔር ዘንድ እሣት መጥቶ አዛዥን እና ወታደሮቹን አቃጠላቸው፡፡ 13 ንጉሡ ይህን ሲሰማ እንደገና አንድ አዛዥ እና አምሳ ተጨማሪ ወታደሮችን ላከ፡፡ ኤልያስ ወደነበረበት ሥፍራ ሄዱ አዛዥ በኤልያስ ፊት ለፊት ቆመና ነቢዩ እለምንሀለሁ እሳክህ እኔን እና አምሳዎቹን ወታደሮቹን አትግደለን 14 ሦስት ጊዜ እሣት ከሰማይ ወርዶ አዛዦችን እና ከእነርሱ ጋር የነበሩ ወታደሮችን እንደገደለ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ አሁን እባክህ ራራልኝ አለ፡፡ 15 ያኔ ከእግዚአብሔር የተላከ መልዓክ ለኤልያስ እንዲህ አለው ወደታች ውረድና ከአዛዡ ጋር ሂድ አትፍራው ስለዚህ ኤልያ ከወታደሮቹ ጋር ወደ ንጉሡ ሄደ፡፡ 16 ኤልያስ ወደሄደበት ሥፍራ ሲደርስ ንጉሡን እንዲህ አለው ይህን ነው እግዚአብሔር የሚለው የምትድን ወይም የማትድን መሆንህን ለመጠየቅ መልዕክተኞችን ወደ ኤክሮን አምላክ ብዔልዘቡል ላካህ፡፡ የሚያማክር አምላክ እሥራኤል ውስጥ የሌለ አስመሰልክ፡፡ ስለዚህ ከቁስልህ አትድንም እንደውም ልትሞት ነው፡፡ 17 ስለዚህ አካዝያስ ሞተ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ይሆናል ብሎ ለኤልያስ የነገረው ነው የአካዝያስ ታናሽ ወንድም ኢዮራም አዲሱ ንጉሥ ሆነ ይህም የሆነው የኢዮስፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነው የአካዝያ ወንድም ንጉሥ የሆነበት ምክንያት አካዝያ ንጉሥ የሚሆን ወንድ ልጅ ስላልነበረው ነው፡፡ 18 አካዚያ ስለ አደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ ለማወቅ ከፈለጋችሁ የእሥራኤል ነገሥታት ሥራዎች በተጻፉበት መጽሐፍት ውስጥ ይገኛሉ፡፡