1 ብህም እረን ኢየሱስ በጀልበይ ደር ሃናም የባሳይ መይ ቡረደም የጋጋን ደብር መጥ፡፡ 2 በጅም ሰብቻይ በአልጋይ ደር እኝም የል ሀድ እንጅንዋ እንግርን የሰለል ሰብ እንዚም የኢየሱስን አምጢ፡፡ ኢየሱስም እምነተዋም እሪም እንጅንዋ እንግርን ለሰላሌይ ሰብቻ ‹‹ በዩያ አይዝህ ዲርጎትህ ታደግነሃት ›› በሌይ፡፡ 3 በውትም ሀደዲ የሙሴይ ሕግ አስተማረሩ ‹‹ እህይ ሰብ በእግዜር ደር አይኩ የሰድቤይ ቃል የወሊሃል ›› ትይቡሉ በደልዋም እሰብ፡፡ 4 ኢየሱስም አሰባኖም ቻ ላም ኡኩ በሏሙ ‹‹ ለምነን እህኔይ በዱ ሰነን በደልሁም ቶሶቦሁም ›› 5 ገጋን ‹‹ ዲርጎትህ ታፋቀንሃማ በቡይትዋ ንቅም አሶምድ በቡይት አይቴይ ይቀልለል? 6 በውትም በቀር የሰብ በዩ በደቺይ ደር ዲርጎቴይ ልያትፍቅ ሥልጣን የለይሁም ወቻሊን አለህብሁማ በላም እንጅንዋ እንግረን የሰሎላይ ሰብቻ ‹‹ አልጋህ ጡርም የገረህ ሂድ ›› በለይ፡፡ 7 ኡትም ነቀም የጋረን ሂድ፡፡ 8 ሕዝብም እህኔይ በሩይግ ተደኖቁ፤ እኩ የሃን ሥልጣን ለሰብ በወቡትን እግዜረን አምሰጎን፡፡ 9 ኢየሱስም በውት አውደ ነቀም ትይሂድ ተል ማቲዎስ ይትብለላይ ግብረይቢ ሰበሶባለይ አውደ ተጉቢም ታል ረሃቤይም ‹‹ ታህታለኝ›› በለይ፣ ማቴዎስም ነቀም ተህታለይ፡፡ 10 ኢየሱስ በማቴዎስ ጋር በማዕድ ተጉብም ተል ብዝ ግብር ይስቦሰበለይዋ ዲርጎታኘኙ አጅ ሞጦም ቶውትዋ ተታማረሩን በድ በማዕድ ተጉቡ፡፡ 11 ፈሪሳሱም እህኔይ ኡሩም ለተማረሩን ‹‹ አስተማርሁም ግብሬይ ትይሰቦሱባለይዋ ተዲርጎተኛኙ በድ አይኩ ይበላል ›› ቦሉም፡፡ 12 ኢየሱስም እኔይ ሰማም እኩ ትይብል አግረገበኖም ‹‹ እደባተኛኙይ በቀር ፋያ ለሆንይ ሐኪም አያትፋጬሙ፡፡ 13 ሁድ ኤየ እፋጭየሎህ ምህረትን በቀር እንኩ ይቀርበል ሰነኑ ተበኝም የፀፌይ ምን የሃኔይንሁም ኡሩ፡፡ ኤየ የመጠህይ ደርጎተኘኙን የንስሐ ለሊጣሮም በቀር ፀድቀኔይ የንስሐይ ልሊጣሩ፡፡ 14 ኡህምነምግ የዮሐንስ ተማረሩ የኢየሱስን ምጠም ‹‹ እኛዋ ፈሪሳሱይ ሁለምግ ትልሰምንን የሃቴይ ተማረሩ ለምነን አይሰሙት? 15 ኢየሱስ ኡኩ ትይብል አግረገበኖም ‹‹ ሙሽሩይ ቱኖሙ በድ ተል ሚዘዙይ ዮዝንን አሰቦሙማል? ለሃነምግ ሙሸሩይ ቱዋሙ አደዴ ይሙጠለግ የመጠል፤ ኡህምነግ ይሃናል፡፡ 16 አኩም በእብሪ ልበሻ ደር መይ የሊነከይ ወይራ ወጬ ይትፋል አሎ፤ ማህኛምን ወይረይ ወጬ የእብሬይ ልባሻ ደቡጭቅም ቃዋን የባሰ ያሳፋይል፡፡ 17 አኩም በቢጌ የምይ ሲልቻ ወይረ የወይሄይ ሲሐር ይሃትታል እሎ፤ እህኔይ ይሰነልላላግ አህም የመይ ሲልቻ ይትረታረል፤ የወይንም ሰሐት ይትሁዳል ሲልቻም ይትበለሸም የይጠቅም ይሃናል፡፡ ለሃነምግ የወይረይ የወይን ስሐሬይ በወይራ ሲልቻ ዩህተገን አለማ፤ ብህም አከሌት ሆይትኖም ሀድ ሀዴዱ ወቅረረትን አለብማ፡፡ 18 ኢየሱስ እህኔይ ትይድም ተል ሀድ የምኩረብ አለቃ ዮውትን ሀድ መጥ፤ ተጋዥም በአንገትን ለኢየሱስ ቀደም ሶጐዱም ‹‹ ዩካ በዩያ ሙታብኛማ፣ ለሃነምግ አተ ብትመጠም እንጅሄይ ብትሃትትባ ትሰሊጢናቱ በሌይ፡፡ 19 ኢየሱስም ነቀም ሰብቻይ ተህታለመ ሂድ፣ ተማረሩምን ተውት በድ ሂዱ፡፡ 20 ዩካ አሥራ ሆይት እዱ ሙል ድም ትይፈሰዋ ትትሰቀይ የነሪት ሀድ ሴት ኡህነምግ፣ልበሸን ጫፋን በእንጅና ነከት፡፡ 21 እህነም የሰንቴይ ‹‹ ልበሸን ጫለ በእንጀያ ለነካግ ዩይናሁ በትም በደልና እሳብትም ለናሬይንው፡፡ 22 ኢየሱስም ግረገባም እረም ‹‹ አይዞሽ በዩያ እምነትሽ አትዩሻጽ ›› በለ ሴትቲም ኡነምግ ኡዩት፡፡ 23 በውትም እረን ኢየሱስ የምኩረቤይ አለቃ ገር በጅጅግ የሐዘኔይ ጡሩንባ ይነፋም ሙሸይ ትያወጡ ኡ ቧሉም ይበቻልይ ሰብቻ እሪ፡፡ 24 ኡከ በል ‹‹ ሁልምሁም ብጅ ውጡ ባዩይ እጀትማል በቀር አልሙትቱ ›› ኡኖሙም አህም ቀሊዲቢም ሶቁቢ፡፡ 25 ሰብቻም በወጡ እረን ኢየሱስ በዩታይ የለተቢይ ገር ገብ፤ እንጅምና ብይዝ ነቅት፡፡ 26 ይህም ሰነን እዝን በውት ደብር ሁልምን ሳም፡፡ 27 ኢየሱስ በውት አውደ ነቀም ተይሂድ ሆይት እኖም የይር ተህቶል፤ እኖሙም ‹‹ የዳዊት በዩያ አደረንህ ማረን›› ትይቡሉ ኡ ዩቡል ናሮ፡፡ 28 ኢየሱስ በገር የገበይግ እኖም የይሪይ የውትን ቆሮቡም፤ ኢየሱስም ‹‹ ኤያ እህኔይ ወሳን አቀትላሎሁም ቆሙ ኖረም? በሏሙ፡፡ እኖሙም ‹‹ ኦ ጎይታዬ ›› ትይቡሉ አግሮጎቡን፡፡ 29 በውትብ እረን ኢየሱስ ኢናኖም በእንጅን እንዘዘም ‹‹የእምነቶሁም›› የሃኑሁም በሏሙ፡፡ 30 ኢኖም ተከፋት፣ ኢየሱስም ‹‹ ለሀድምን አቴደ ትይብል አጣበቃም እዛዞም፡፡ 31 ኡኖሙም አህም ሂዱም በውት ደብር በሁልምን አውደ የኢየሱስን ግዲርነችዋ እዝን አወጡም እዱ፡፡ 32 ኢኖሚ የትካፋ ተኖሙይ ሰብቻ ወጡም በሂዱግ ሊለቹ ሰብቻ አህም ጋኔል የንደረብይ ዱደ የኢየሱስን ሀድ አምበሪ፡፡ 33 ጋኔል በወጠን እረን ዱዳይ ሰብቻ አወለህ፣ ሕዝብም ‹‹ እኩ ያል ሰነን በእስራኤል ሀድ ታሪም አይቹሊ ›› ትይቡሉ ተደኖቂ፡፡ 34 ፈሪሳሱም አህም ‹‹ ኡት ጋኔሌይ የወጣለይ በጋኔልን አለቃ ሳበቡ›› ቦሉ፡፡ 35 አኩም ኢየሱስ በምኩረብዋ ትየትምር የእግዜርን መንግሥት ቤይዘይ የምሥራቹይ ቃል ትየስም ሕዝባም በእዳባትንዋ በአዜሁሉን ሁለምን ትየትዬ በከተማኖምዋ በመንደረርቻኖም ሁልምን ትትግረገብን ናሮ፡፡ 36 ሕዝቢ ዘቁ 1ኛ የልለይሁም ጠቀቅቻ ተጮኖቁ ምዋ ቁባ ይሃኖማል በቆበጥግ እሪም አዘናኖም፡፡ 37 ልህም ለተማረሩን እኩ በሏም ‹‹ መከር ብዝኑ ብለተኘኙይ አህም ጢትኑ፡፡ 38 አኩም ይዳበለሊ ብለተኘኙ ለመከር ብል ልይልህ የመከሬይ ጎይታ ጡቆስ፡፡